Wednesday, 4 May 2016

1 ሐዲሶች ስለ ረመዳን

No comments:

ሐዲሶች ስለ ረመዳን

ፆመኛ የሆነ ሰው በቀን በከፊልም ሆነ በሙሉ አካላቱን ቢታጠብ ፆሙ አይበላሽም ፡፡

--
ረሱልም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በረመዳን ከፈጅር በፊት ከግንኙነት በኋላ ገላቸውን ሳይታጠቡ (ጁኑብ) ሆነው ከፈጅር በኋላ ገላቸውን ታጥበው ፆመዋል ፡፡
                                                         
--
ከሰሐባዎች አንዱ ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ፆመኛ ሆነው ጥም ወይንም ሙቀት ለማስወገድ በጭንቅላታቸው ላይ ውሃ ያፈሱ ነበር ብሏል ፡፡

(
አቡዳውድ ዘግበውታል። ሸይኽ አልባኒ ሰሒህ ብለውታል። )

قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : " من لم يبيت الصيام من الليل فلا صيام له "
 رواه أبو داود (ص 219)

የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እነዲህ ብለዋል።

"ከለሊቱ ከፍለ ጊዜ(ከፈጅር በፊት) የፆምን ኒያ ያላሳደረ ፆም የለውም።) 

አቡዳውድ ዘግበውታል። አልባኒ ሰሒህ ብለውታል።

ከተረሱ የነቢያችን(ዐለይሂ ወሰለም) ሱናዎች መካከል፦

ከዊትር ሰላት በኋላ የሚባል ዱዓ   "ሱብሓነል መሊኪል ቁዱስ"
(3
ጊዜ)

ሦስተኛው ላይ መድ ወይም ሳብ ይደረጋል።
ሱብ____


ተራዊህ ላይ ኢማሙ ሲያሰግድ በቁርኣን መከታተል!

No comments:
ተራዊህ ላይ ኢማሙ ሲያሰግድ በቁርኣን መከታተል!

ጥያቄ፦

በተራዊህ ሰላት ውስጥ ኢማሙን ለመከታተል በማለት ማእሙሞች ቁርአን መያዛቸው እንዴት ይታያል?

መልስ፦

 ለዚህ አላማ ብሎ ቁርአንን መያዝ ሱናን መፃረር ነው። ይህም በተለያየ መልኩ ነው፦

አንደኛ፦ በቂያም ላይ ሰውየው ቀኝ እጁን ግራ እጁ ላይ ማድረጉ ይቀርበታል።

ሁለተኛ፦ አስፈላጊ ላልሆኑ እንቅስቃሴዎች ይዳርጋል። እነሱም፦ ለምሳሌ ቁረአንን መክፈት፣ መዝጋት፣ በብብት ሥር ወይም በኪስ ማድረግና የመሳሰሉት ናቸው።

ሦስተኛ፦ እነዚህ እንቅስቃሴዎች የሰጋጁን ትኩረት ያዛባሉ።

አራተኛ፦ ሰጋጁ የሱጁድን ቦታ መመልከቱ ያመልጠዋል። አብዛኛዎቹ ዑለሞች እንደሚሉት ደግሞ በሰላት ጊዜ የሱጁድን ቦታ መመልከት ሱናና በላጭ ነው።

አምስተኛ፦ ይህን የሚያደርግ (ቁርአንን የሚይዝ) ሰው ልቡ ወደ ሌላ ቦታ ካሰበ ሰላት ውስጥ መሆኑን ሊረሳም ይችላል። በአንፃሩ ቀኝ እጁን ግራ እጅ ላይ አድርጎና አንገቱን ሰብሮ ወደ ሱጁድ ቦታ እየተመለከተ በኹሹዕ ከቆመ ግን ልቡን ለመሰብሰብና ከኢማም ሗላ ሆኖ በመስገድ ላይ መሆኑን ለማስታወስ በጣም ቅርብ ነው።


(ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ረሒመሁላህ)

የቁርኣን ሰዎች ማናቸው?

No comments:

የቁርኣን ሰዎች ማናቸው?

ሸይኽ ሳሊሕ አልፈውዛን እንዲህ ይላሉ:-

‹‹የቁርኣን ሰዎች ሲባል የሚፈለገው የሚያፍዙት፣ በሥርዓት የሚያነቡት ወዘተ ••• ማለት አይደለም። የቁርኣን ሰዎች የሚባሉት ባያፍዙት እንኳን የሚሰሩበት ናቸው። እነዚያ ትእዛዛቱን የሚፈፅሙ፣ ክልከከላውን የሚርቁ፣ ከወሰኑ የሚቆሙ እነሱ ናቸው የቁርኣን ሰዎች። እነዚህ የአላህ ሰዎች ናቸው፣ ከፍጡሩ ልዩዎቹ! ቁርኣንን አፍዞ፣ አሳምሮ የሚቀራና ሑሩፎቹን አስተካክሎ እያነበበ ነገርግን ድንጋጌዎችቹን የሚጥስ የሆነ ሰው ይሄ የቁርኣን ሰው አይደለም። ከአላህ ልዩ ሰዎች ውስጥም አይደለም። ይልቁንም ይሄ አላህና መልእክተኛውን የሚያምፅ ቁርኣንንም የሚፃረር ነው። 

 
አዎ! የቁርኣን ሰዎች በተጨማሪ እነዚያ ማስረጃ የሚያደርጉት ናቸው። በማስረጃ አጠቃቀም ላይ በሱ ላይ ሌላን የማያስቀድሙ ናቸው። ፊቅሁንም አሕካሙንም በጥቅሉ ዲናቸውንም ከሱ ይወስዳሉ። እነዚህ ናቸው የቁርኣን ሰዎች። 

ሸርሑ ኪታቢ አልዑቡዲያህ
 
back to top