Wednesday, 4 May 2016

ፈጥነው ያፍጥሩ ባይሆን አደጋ ላይ እንዳይወድቁ ይጠንቀቁ!

No comments:

ፈጥነው ያፍጥሩ ባይሆን አደጋ ላይ እንዳይወድቁ ይጠንቀቁ!

ፊጥራን ማፋጠን ከኢስላም መገለጫዎች አንዱ ከመሆኑም በላይ ታላቅ ደረጃ ያለው ሱናህ ነው፡፡
 ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፡-

ፊጥራን እስካፋጠኑ ድረስ ሰዎች ከመልካም ነገር አልተወገዱምይላሉ፡፡

ስለዚህ አደራዎትን እንደ ቀላል በማየት ይህን የመሰለ ድንቅ ሱናህ እንዳያሳልፉ፡፡ ባይሆን ይጠንቀቁ፡፡ ሲያፈጥሩ ፀሀይ መግባቷን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ ፊጥራን ማፋጠን ማለት ወቅት ሳይገባ ማፍጠር ማለት አይደለምና፡፡ እናም ቀኑን ሙሉ የዋሉበትን ፆም ፀሀይዋ ሳትገባ አትቀርም በሚል ጥርጣሬ እንደዋዛ እንዳያፈርሱ ይጠንቀቁ፡፡

አልኢማም ኢብኑ ዐብዲልበር ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- 

ፊጥራን ማፋጠን ሊሆን የሚገባው ፀሀይ መግባቷን ካረጋገጡ በኋላ ነው፡፡ ለማንም ቢሆንፀሀይ ገብታለች ወይስ አልገባችም? እያለ የሚጠራጠር ሆኖ ሳለ ሊያፈጥር አይፈቀድለትም፡፡ ምክንያቱም ግዴታ (ዒባዳህ) በእርግጠኝነት ከተያዘ በጥርጣሬ ከሱ አይወጥጣምና፡፡ አሸናፊና የላቀው አላህ (ከዚያም ፆሙን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉት) ይላል፡፡ የሌሊቱ መጀመሪያ ደግሞ የፀሀይ ከተመልካቾች አይን ሙሉ ለሙሉ ከአድማሱ ውስጥ መግባት ነው፡፡ የተጠራጠረ መጠበቅ የግድ ይለዋል፣ በመግባቷ ላይ እስከማይጠራጠር ድረስ፡፡


[አትተምሂድ፡ 7/181]

No comments:

Post a Comment

 
back to top