Wednesday, 4 May 2016

ሰለፎቻችን ቁርዓንን እንዴት ነበር የሚቀሩት?

No comments:

ሰለፎቻችን ቁርዓንን እንዴት ነበር የሚቀሩት?

        ከፊሎቹ በየወሩ ሌሎቹ በየአስሩ ቀናት ሌሎቹም በየስምንት ወይም በየሰባት ቀናቱ ያከትሙ ነበር፡፡ ኡስማን ኢበኑ አፋን፣ተሚሙዳሪ፣ ሰዒድ ብኑ ጁበይር፣ ሙጃሂድ አና አል-ኢማሙ ሻፊዒይ በአንድ ቀንና ሌሊት ሙሉ ቁርዓን ያኸትሙ እንደነበር፤ አብዛኛዎቹ ሰለፎች ግን በየሰባት ሌሊት እንደሚያከትሙ ኢማሙ ነወዊ ገልፀዋል፡፡

ቁርዓን መቅራት የሚወደድባቸው ጊዜያት አሉትን?

ኢማሙ ነወዊ እንደገለፁት ለመቅራት በላጩ ሁኔታ በሰላት ውስጥ ሲሆን በሌሊት የመጨረሻው ግማሽ ሌሊት ደግሞ ከመጀመሪያው የተሻለ ነው፡፡ በኢሻ እና በመግሪብ መካከልም መቅራት የተወደደ ነው፡፡ ሰላት በተከለከሉበት ወቅቶች ቢሆንም እንኳን፡፡ እንዲሁም በረመዷን ቁርዓን ማብዛት አለብን የቁርአን ወር ነዉና፡ በተለይም በመጨረሻዎቹ አስር ቀናቶች ከአስሮቹ ደግሞ በነጠላዎቹ (21 23 25……..) እንዲሁም በመጀመሪያዎቹ የዙልሂጃ አስር ቀናት በተለይም በዓረፋ ቀን ቁርአን መቅራትን ልናበዛ ይገባል፡፡
እነዚህ የተመረጡ ጊዜያት ናቸው፡፡

አላህ ከቁርአን ህዝቦች ያድርገን
www.nesiha.com



No comments:

Post a Comment

 
back to top