ፆምን የሚያበላሹ
ነገሮች!
ፆመኛው
ፆምን የሚያበላሹ ነገሮችን
ረስቶ ወይም ተገዶ
አሊያም ባለማወቅ አንዱን
ቢፈፅም ፆሙ አይበላሽም፡፡ ይህም
በተከታዮቹ ቁርአናዊ መረጃዎች መሰረት
ነው፡፡
رَبَّنَا لاَ تُؤَاخِذْنَا
إِن نَّسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَا - البقرة: ٢٨٦
((…(በሉ)፦ ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን (አትቅጣን)…)) {አል-በቀራህ፡286}
إلا من أكره وقلبه مطمئن بالأيمان - النحل: ١٠٦
((..ልቡ በእምነት የረጋ ሆኖ (በክህደት ቃል በመና
ገር) የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር)) {አል-ነህል፡106}
وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ
جُنَاحٌ فِيمَا أَخْطَأْتُم بِهِ وَلَٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ -
الأحزاب: ٥
((በርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም
በናንተ ላይ ሀጢአት
የለባችሁም፤ ግን ልቦቻችሁ አውቀው
በሰሩት (ሀጢአት አለባችሁ)…))
{አል-አህዛብ፡5}
- ስለዚህ ፆመኛው
ረስቶ ቢበላ ወይም
ቢጠጣ ሆን ብሎ ባለመሆኑ ፆሙ አይበላሽም፡፡
- ፀሀይ መጥለቋን ወይም ጐህ ያለመቅደዱን በማሰ ብ ቢበላ አሊያም ቢጠጣ ፆሙ አይበላሽም፡፡ ምክን ያቱም እውነታውን ባለማወቁ ነው፡፡
- ፆመኛው በመጉመጥመጥ ላይ ሳለ ሳያስበው ውሃ ወደ ጐሮሮው ቢወርድ አስቦት ባለመሆኑ ፆሙ አይበላሽም፡፡
- ፆመኛው በእንቅልፉ ላይ ሳለ ፍትወት ቢፈሰው ፆሙ አይበላሽም፡፡ ምክንያቱም በፍላጐቱ የተከሰተ ባለመሆኑ ነው፡፡
ፆምን የሚያበላሹ (የሚያፈርሱ)ነገሮች ስምንት ናቸው፡፡
እነርሱም፦
እነርሱም፦
1/ የግብረስጋ ግንኙነት የረመዳንን ፆም መፆም ግዴታነት የፀናበት ፆመኛ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የግብረስጋ ግንኙነት ከፈፀመ በዚህ ድርጊት ምክንያት ፆም ይፈታል፡፡ በመሆኑም ይህንን ዕለት በሌላ ጊዜ መፆሙ ግዴታ ከመሆኑም ጋር ማካካሻ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ማካካሻውም ባርያን ነፃ ማውጣት ካላገኘም ሁለት ወራትን በተከታታይ መፆም ይህንም ካልቻለ ስልሣ ምስኪኖችን ማብላት ነው፡፡
2/ ብልትን በመነካካት ወይም ከተቃራኒ ፆታ ጋር በመተሻሸት ወይም በመሳሳም አሊያም በመተቃቀፍ እና በተመሳሳይ ሁኔታዎች ፍትወትን ማፍሰስ፡፡
3/ እንደ ሲጋራ ያሉ ነገሮችን መጠቀምም ይሁን ሌሎች የሚጠቅሙም ሆነ የሚጐዱ ነገሮችን መብላት ወይም መጠጣት፡፡
4/ ምግብን ሊተኩ የሚችሉ ሀይል ሰጪ መርፌዎችን መወጋት ፆምን ያበላሻል፡፡ ምክንያቱም እንደነዚህ አይነት መድሃኒቶች ሙሉ በሙሉ የምግብ አይነት ጥቅም ሊሰጡ የሚችሉ ከመሆናቸው ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የምግብነት ባህሪ የሌላቸውን መድሃኒቶች በመርፌ በጡንቻ ወይም በደም ስሮች ላይ በመወጋት መጠቀም ፆምን አያበላሽም፡፡ በ ጉሮሮው ውሰጥ የጠብታው ጣዕም ቢታወቀውም እንኳ ፆሙ አይበላሽም፡፡
5/ ደምን መውሰድ ይህም ማለት ለምሳሌ አንድ ፆመኛ ደም ቢፈሰው እና ምትክ ደም መውሰድ ቢያስፈልገው ፆሙ ይበላሻል፡፡
6/ የወር አበባ እና የወሊድ ደም መፍሰስ፡፡
7/ በዋግምት እና በመሳሰሉት መንገዶች ደምን ማስወጣት፡፡
8/ ሆንብሎ (እጅን እና መሰል ነገሮችን በመጠቀም) ማስታወክ (ማስመለስ) ሲሆን ነገር ግን ግለሰቡ ከቁጥጥሩ ውጪ ሆኖ ቢያስመልሰው ፆሙ አይበላሽም፡፡
��ሼር በማድረግ ይተባበሩ

No comments:
Post a Comment