አሰላሙ ዐለይኩም
<<ለረመዷን፥ ተዘጋጅተዋል?? በምን ይሁን የተዘጋጁት>>
ረመዷን ሲመጣ ሰዎች መዘጋጀት ይጀምራሉ ነገር ግን የሁሉም ዝግጅት አንድ አይነት አይደለም::
ከፊሎች በምግብ ሲዘጋጁ ሊሎች ደግሞ በልብስ ( ጀለቢያ ሽርጥ ጥምጣም ኮፊያ አባያ ሸርሸፍ ወዘተ) ይዘጋጃሉ እነዚህ ብዙም የማያስወቅሱ ሲሆን ሌላ ጥቂት የማይባሉ ደግሞ ሸይጧናዊ ዝግጅት ያደርጋሉ= የሱዳን ዘፈን የሶማሌ ከበሮ አዘል ዜማ በሽርክና ቢድዓ የተሞላ መንዙማ የሙዚቃ መሳሪያ የተቀላቀለበትና በጋራ (አንዳንዴም በሴቶች ወይም ከሴቶች ጋር የሚዘጋጅ) ነሺዳ ስም-ኢስላም ፊልም እና ድራማ ወዘተ ይዘጋጃሉ::
እነዚህ ከላይ እንደተባለው -ሸይጣናዊ ዝግጅታቸው- በጣም ያስወቅሳቸዋል:: በረህመትና በቁርአን ወር ሰዎችን ከአሏህ ቃል (ቁርኣን) እንዲርቁ ከማድረግ የበለጠ << ሸይጣናዊ የሚያስብል ተግባር አለ እንዴ ??!! >>

No comments:
Post a Comment